





የከለላ ወረዳ አይሲቲ ልማትና ማስፋፊያ ዋና የስራ ሒደት የሚገኘው በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን መስተዳደር በከለላ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ስር የሚገኝ ሲሆን ይህ ስራ ሒደት ከተቋቋመበት አላማ አንጻር ዘርፈ ብዙ ስራዎች ቢኖሩትም ለብዙ በጥቂቱ በወረዳ ደረጃ የሰው ሃይል ልማት ላይ፣በኔትወርክ መሰረተ ልማት ላይ፣ተዘዋዋሪ ችሎት በፕላዝማ መስጠት ላይና የተለያዩ ወጪ ቆጣቢ ሆኑ አሰራሮችን ለወረዳ በሚጠቅም መንገድ በመቀየር ወረዳ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ የሚሉትና ሌሎችም ይጠቀሳሉ ። ከለዚህ አንጻርም የወረዳችን ሴክተር መ/ቤቶች አበረታች በሆነ መንገድ አይሲቲን እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። በቀጣይም የኔትወርክ ሽፋናችንን 100% በማድረስ ወረዳችንን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዘል።
ድህረ ገጽ ግንባታ ላይ በ2006 ዓ.ም እንደ ስራ ሒደታችን ያቀድነው የአስተዳደር ጽ/ቤትንና የስራ ሒደታችንን ድህረ ገጽ ከክፍያ ነጻ በሆነ መንገድ በመጠቀም የሌሎችን ሴክተሮች ከዚህ ተነስተን የድህረ ገጽን አስፈላጊነትና በክፍያ ደረጃ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ካሰለጠንን በኌላ በ2007 በጀት ዓመት የሴክተሮችን ድህረ ገጽ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ዲዛይን በማድረግና ከቴሌ ጋር በመነጋገር የየሴክተሮችን ድህረ ገጽ የማስለቀቅ ስራ እንሰራለን።
የአይሲቲ ልማትና ማስ/ዋ/የስራ ሒደቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴት
ራዕይ (Vision)
በሚቀጥሉት 15 ዓመታት የሁሉም የከላላ ሕዝብ ኑሮና ህይወት በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ ሆኖ ማየት፣
ተልዕኮ (Mission)
ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን በወረዳው በማልማት፣ በማስፋፋት፣ በመጠቀምና የህብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል ለልማትና መልካም አስተዳደር መጐልበት የሚሰጠውን ድጋፍ ማሳደግ፣
እሴቶችና የአሰራር መርሆዎች (Value and principles)
እሴቶችና የአሰራር መርሆዎች (Value and principles) የስራ ሂደቱን ዓላማ በማሳካትና የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት የሚከተሉትን እሴቶች በማጐልበት ይጠቀምባቸዋል፡፡
Ø ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎነትን እናረጋግጣለን፣
Ø ለደንበኞች እርካታ ቅድሚያ እንሰጣለን፣
Ø ምርጥ ተሞክሮን እናስፋፋለን፣
Ø ከኢኮቴ ዕድገት ጋር እንራመዳለን፣
Ø ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን፣ አሳታፊነትን እናረጋግጣለን፣
Ø ቡድናዊ የስራ መንፈስን እናሰፍናለን፣